Skip to this page's content

KCHA's Section 8 waiting list lottery application open until Feb. 25

Find a Home

In This Section

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች የKing County Housing Authority 2020 ንዑስ ክፍል 8 ተጠባባቂዎች ዝርዝር

ይህ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች በKing County Housing Authority ንዑስ 8 ለማመልከት (ቤቶች የመምረጫ ቫውቸር) ተጠባባቂዎች ዕጣ ዝርዝር ላይ ያለዎትን ጥያቄ ይመልሳል ብለን እናምናለን፡፡ ጥያቄዎን እዚህ ካልመለስን ወደ ንዑስ ክፍል 8 206-214-1300 ከ ሰኞ እስከ አርብ ከ 9 AM እስከ 4 PM ድረስ እባክዎ ይደውሉ፡፡

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የKCHA ጥያቄዎችን ሊታተም በሚችል የፒዲኤፍ (PDF) ፋይል ያውርዱ፡፡

የንዑስ 8 ተጠባባቂ ዝርዝር ዕጣ መቼ ይከፈታል?

የሚከፈተው በፌብሪዋሪ 12፣ 2020 በ7:00 AM እና የሚዘጋው ደግሞ በፌብሪዋሪ 25፣ 2020 በ4፡00 PM ነው፡፡

ምን ያህል አመልካቾች ተቀባይነት ያገኛሉ?

ሁሉም የንዑስ 8 ብቁ የሆኑና በሰዓቱና በቀኑ ያስገቡ አመልካቾች ተቀባይነት ያገኛሉ (በቤት አንድ አመልካች ብቻ የተወሰነ ነው)፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ከታች ንዑስ 8 ብቁ የሆኑ ይመልከቱ፡፡

ማመልከቻችሁን ከሞላሁ፣ የንዑስ 8 ቫውቸር እቀበላለሁ?

ማመልከቻውን መሙላት ብቻ የንዑስ 8 ቫውቸርን ለማግኘትዎ ማረጋገጫ ዋስትና አይሆንም፡፡ ማመልከቻዎ ከሌሎች አመልካቾች ጋር እንዲመደቡና ከእነዚያም ውስጥ 2500 እድለኛ የሆኑ ሰዎችን መርጠን በቫውቸር ተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም፣ ቫውቸር ለመቀበል፣ ቤተሰብዎ ለንዑስ 8 ብቁ መሆን አለበት፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ከታች ንዑስ 8 ብቁ የሆኑ ይመልከቱ፡፡

በተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ መግባት አለመግባቴን መቼ ነው ማወቅ የምችለው?

እድለኛ ሆነው ለአዲሱ ተጠባባቂዎ ዝርዝር ከተመረጡ በኢሜል፣ በጽሁፍ መልዕክት፣ ወይንም በደብዳቤ እናሳውቃለን፡፡ ማሳወቂያው በማርች 31 ይላካል፡፡ በምርጫ ሂደቱ ላይ አዳዲስ መረጃ ለማግኘት https://www.kcha.org መመልከት ይችላሉ፡፡ በማርች 31 ኢሜል፣ የጽሑፍ መልዕክት ወይንም ደብዳቤ ካልደረስዎት እባክዎን ይደውሉልን፡፡

ማመልከቻውን ካስገባሁ በኋላ የምገኝበት አድራሻ ከተቀየረ ለኬኤስኤችኤ (KCHA) እንዴት ማሳወቅ እችላለሁ?

የማመልከቻ ጊዜ ሰሌዳው ካለፈ በኋላ የሚገኙበትን አድራሻ መቀየር ከፈለጉ ኦንላየን በ kcha.org ላይ በመሄድ ወይም በፖስታ መቀየር ይችላሉ፡

KCHA
Attention: Section 8 Applications
700 Andover Park West
Tukwila, WA 98188

የሚገኙበት አድራሻ ላይ ለውጥ ካለ በተቻለ ፍጥነት ለኬሲኤችኤ (KCHA) ያሳውቁ ( የስልክ ቁጥርዎ፣ የመልዕክልት ሳጥን ቁጥርዎ፣ ወይንም የኢሜል አድራሻዎ)፡፡

ለንዑስ 8 ተጠባባቂ ዝርዝር ዕጣ እንዴት ማመልከት እችላለሁ?

አንዴ የዕጣ እድሉ ክፍት ከሆነ የማመልከቻውን ማስፈንጠሪያ በ https://www.kcha.org/lottery ሲጫኑ ወደ WaitListCheck.com ይወስድዎታል፡፡ ማመልከቻው በኦንላየን የሚሞላ ብቻ ነው፡፡ ምንም ዓይነት በወረቀት የሚሞላ ማመልከቻ የለም፡፡

ለማመልከት የሚከፈል ነገር አለ?

የለም፡፡ ለንዑስ 8 መርሃ ግብር ማመልከት ምንጊዜም ነጻ ነው፡፡ ገንዘብ የተጠየቁ እንደሆን በ King County Housing Authority ወይንም የ WaitListCheck ድረገጾች ላይ አይደሉም ማለት ነው፡፡ ለንዑስ 8 ተጠባባቂዎች ዝርዝር ዕጣ ማመልከቻ ለማስገባት የሚጠቀሙበት ማስፈንጠሪያ kcha.org/lottery ይህ ብቻ ነው፡፡

ለዕጣው ለማመልከት ምን ዓይነት መረጃ ያስፈልገኛል?

በማመልከቻው ላይ የሚከተሉትን መረጃዎችን እንጠይቅዎታለን፡፡

 • በቤትዎ ውስጥ ስለሚኖሩ እያንዳንዱ ግለሰብ: ስም, ከእርስዎ ጋር ያላቸው ዝምድና, የትውልድ ቀን, የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር (አስፈላጊ ከሆነ), ዘር/ ብሔር፡
 • ለቤቱ ወርሃዊ ገቢ ( ወርሃዊ ገቢ፣ የጥቅማ ጥቅም ገቢ፣ የአካል ጉዳተኝነት ጥቅማ ጥቅም፣፣ የሕጻናት ድጋፍ አገልግሎት ወዘተ.)፡፡ ቀጣሪዎችዎ የሚገኙበትን አድራሻ መረጃ መስጠት ይጠበቅብዎታል፣ ካለዎት፡፡
 • አሁን የሚኖሩበት ቤት የሚገኝበት ሁኔታ (የት እንደሚኖሩ፣ ለቤት ኪራይና ለውሃ ለመብራት ምን ያህል እንደሚከፍሉ)፡፡
 • የሚገኙበት አድራሽ (ኢሜል፣፣ ስልክ፣ አድራሻ) ስለዚህ KCHA የዕጣውን ውጤት ይነግርዎታል፡፡

ለማመልከት የኢሜል አድራሻ ያስፈልገኛል?

አያስፈልግዎትም፡፡ በWaitListCheck ላይ አካውንት ለመክፈት ማመልከቻውን ለመሙላት በኢሜል ወይንም የስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ፡፡ እርስዎን ለማግኘት አስተማማኙ መንገድ በመሆኑ፣ የሚገኙበት አድራሻ ላይ የኢሜል አድራሻ እንዲሰጡ አጥብቀን እመክርዎታለን፡፡ የኢሜል አድራሻ ከሌለዎት፣ ኢሜል አድራሻ በነፃ መክፈት የሚያስችል በርካታ አማራጭ አለ፤ Gmail, Yahoo Mail, እና Outlook ጨምሮ፡፡

ለማመልከት ቋሚ አድራሻ ያስፈልገኛል?

አያስፈልግዎትም፡፡ ኢሜል ወይንም የስልክ ቁጥር ካለዎት የዕጣውን ውጤት ለመንገር እንጠቀምበታለን፡፡ በዝርዝር ውስጥ ከተካተቱ፣ የሚፈርሟቸውን ቅጾች ለመላክ የፖስታ አድራሻ ስለምንፈልክ ከቻሉ የፖስታ ሳጥን ቁጥርዎን ያካትቱ፡ በአሁኑ ሰአት ቋሚ አድራሻ ከሌለዎት፣ የሚኖሩበትን አካባቢ ስም ሊሰጡ ይችላሉ (መስቀለኛ መንገድ) ወይም “N/A”፡፡

ለማመልከት የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ያስፈልገኛል?

ለማመልከት በቤተሰብዎ ውስጥ ቢያንስ አንድ ሰው የሚያገለግል የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ሊኖረው ይገባል፡፡ በዕጣው መሰረት የእርስዎ ቤት በቫውቸር ተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ ለመስፈር ከተመረጠ የ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር (Social Security Number - SSNs) ቁጥርዎን ለሁሉም አብረዎት ለሚኖሩ ቤተሰቦች ወይንም የቫውቸር ደረሰኝ ከመቀበልዎ በፊት የ SSN ላልተሰጠው ግለሰብ በአጠቃላይ ይፋ ለማድረግ ይገደዳሉ፡፡

ማመልከቻዬን በትክክል ማስገባቴን በምን ማወቅ እችላለሁ?

ማመልከቻውን ሞልተውና አስገብተው ሲጨርሱ በ WaitListCheck ገጹ ላይ “አስገብተዋል (Submitted)” የሚል ያያሉ፡፡ ይህ ቁጥር የሚያረጋግጠው ማመልከቻዎ መግባቱን ነው፡፡ ማመልከቻዎትን ካልጨረሱ፣ የማመልከቻ ጊዜ ሰሌዳው ከመጠናቀቁ በፊት እንደገና ወደ WaitListCheck ገብተው መጨረስ ይችላሉ፡፡

የማመለክትበት ቀንና ሰዓት በተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ያለኝ ዕድል ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል?

አይደለም፡፡ ምክንያቱም ቤቶችን ለመምረጥ የምንጠቀመው በዘፈቀደ ዕጣውን ማውጣት ነው፤ ማንኛውም ያመለከተ ግለሰብ የመመረጥ እና በተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ የመግባት እኩል እድል አለው፡፡ ለማመልከት በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ እስካመለከቱ ድረስ፣ በተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ ለመመረጥ ያለዎትን እድል አይጎዳውም፡፡

በማመለክትበት ወቅት እርዳታ ብፈልግ KCHA እንዴት ላገኘው እችላለሁ?

እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ፣ከሰኞ እስከ አርብ ከ 9AM እስከ 4PM ድረስ ወደ ንዑስ 8 ቢሮ በ206-214-1300 ይደውሉ፡፡ በማመልከቻ ጊዜ ውስጥ በርካታ ስልክ ስለሚደወልልን እባክዎን ይታገሱን፡፡ በተቻለን ፍጥነት ጥያቄዎን ለመመለስ እንሞክራለን፡፡

ማስታወሻ: በማመልከቻ ጊዜው የመጀመሪያ ቀናት በርካታ ስልክ ይደወልልናል፡፡ ስለዚህ የሚፈልጉ ድጋፍ የማመልከቻው ቀን መገባደጂያ ድረስ ሊዘገይብዎ ይችላል፡፡ እባክዎን አስታውሱ! በሚያመለክቱበት ወቅትመቼ በዝርዝ ውስጥ መግባትዎንበጭራሽ አይጎዳውም፡፡

ኮምፒውተር የለኝም፡፡ ኦንላየን ለማመልከት መቼ መሄድ እችላለሁ?

ለማመልከት ማንኛውንም ኮምፒውተር፣ ስማርት ስልክ፣ ወይንም ኢንተርኔት ሊቀበል የሚችል መሳሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡ የ King County Library System ሆነ እና የ Seattle Public Library ለማመልከት የሚረዳዎን ኮምፒውተር በነጻ ይሰጣል፡፡ በሚያመለክቱበት ጊዜ፣ KCHA በአቅራቢያዎ ለማመልከት የሚረዳዎትን ኮምፒውተር ያስቀምጣል ( አዲስ አካበቢ ለማግኘት ደግመው ያረጋግጡ)፡፡

KCHA Central Office, 9AM–4PM (206-214-1300)
700 Andover Park W, Tukwila, WA 98188

Ballinger Homes, 9AM–4:15PM (206-574-1243)
2200 N.E. 201st Place, Shoreline, WA 98155

Birch Creek, 9AM–4:15PM (206-315-4360)
27360 129th Place SE, Kent, WA 98030

Seola Gardens, 9AM–4:15PM (206-829-2465)
11215 5th Ave. SW, Seattle, WA 98146

Spiritwood Manor, 9AM–4:15PM (206-315-4380)
1424 148th Ave. SE, Bellevue, WA 98007

ማመልከቻው ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ውጪ ይገኛል?

ማመልከቻው በእንግሊዘኛ ቢሆንም የ Google Translate እርስዎ ወደ ሚፈልጉት ቋንቋ እንዲተረጉመው ይደረጋል፡፡ Google Translate በትክክል ላይተረጉም እንደሚችል እናውቃለን፡፡ ከእንግሊዘኛ ውጪ ማመልከቻውን መሙላት ከፈለጉ የንዑስ 8 ቢሮን ከሰኞ እስ አርብ ከ9AM እስከ 4PM ድረስ በ 206-214-1300 ይደውሉና በቋንቋዎ የሚረዳዎ ሰው እናዘጋጅልዎታለን፡፡

ለንዑስ 8 ብቁ ነኝ?

ንዑስ 8 ቫውቸር ብቁ ሆኖ ለመገኘት አምስ መስፈርቶችን ማሟላት ያስፈልጋል፡፡ ብቁ ሆኖ ለመገኘት ከጥያቄ ቁጥር 1 እስከ 4 ድረስ ያለውን አዎ፣ ጥያቄ ቁጥር 5 በታች ደግሞ አይ ብለው መመለስ ይኖርብዎታል፡፡

1. ቤቱን የሚያስተዳድረው ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ ነው?

2. ቤትዎ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ቢያንስ አንዱን ይይዛል፡

 • የአካል ጉዳት ያለበት አለ?
 • እድሜው 62 እና ከዚያ በላይ የሆነው አለ?
 • እድሜው ከ18 በታች የሆነው ህፃን አለ?

3. ቤትዎ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው የሚመደብ? “ዝቅተኛ ገቢ” ማለት ዓመታዊ አጠቃላይ ገቢዎ ( ከማንኛውም ታክስ በፊት ወይንም ዊዝሆልዲንግ ከተቀነሰ በኋ) በሰንጠረዡ የተመለከተው ወይንም በታች ከሆነ፡፡

የቤቱ ስፋትአመታዊ ገቢ ልክ ወይንም በታች
1 ሰው$61,800
2 ሰው$70,600
3 ሰው$79,450
4 ሰው$88,250
5 ሰው$95,350
6 ሰው$102,400
7 ሰው$109,450
8 ሰው$116,500
9 ሰው$123,550
10 ሰው$130,650
11 ሰው$137,700

4. ከሚቀጥሉት ሁኔታዎች ቢያንስ አንዳቸው እንኳ ለእርስዎ ይሰራል?

 • ጥሩ እንቅልፍ የማያገኙበት አካባቢ ነው የሚኖሩት? ይህም፡ ደጅ መኖር፣ በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ መኖር፣ ወይንም መኪና ወይንም አርቪ ውስጥ መኖር፡፡
 • ከሚያገኙት አጠቃላይ ገቢ 50 በመቶውን ለቤት ኪራይ እና ለመሰረታዊ ፍጆታ ይከፍላሉ (እንደ መብራት፣፣ ጋዝ፣፣ውሃ፣፣ ቆሻሻ ለማስወገድ)?
 • በቤት ውስጥ ጥቃት ምክንያት፣፣ ክትትል፣፣ ወሲባዊ ትንኮሳ ወይንም በወሲብ ንግድ ምክያት ነው መቀየር የፈለጉት?
 • መቀየር የፈለጉት የሚኖሩበት ቤት ተደራሽ ስላልሆነ ነው፤ በተፈጥሮ አደጋምክንያት፣ በመንግስት ስራወይንም የጥላቻ ወንጀል ተጠቂ ስለሆኑ ነው?
 • በአሁኑ ሰዓት የሚኖሩት ደህንነቱ ባልተጠበቀ ወይንም ባረጀ ቤት ውስጥ ነው? ደህንነቱ ያልተጠበቀ ወይንም ያረጀ ቤት ምሳሌ ማሞቂያው ወይንም የውሃ መስመሩ የማይሰራ ማለት ነው፡፡
 • ቤትዎ በጣም ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው የሚመደብ ነው? “በጣም ዝቅተኛ ገቢ” ማለት የአመታዊ ገቢዎ ከታች የተዘረዘረው ገቢ ወይንም በታች ማለት ነው፡
የቤቱ ስፋትአመታዊ ገቢ ልክ ወይንም በታች
1 ሰው$23,250
2 ሰው$26,600
3 ሰው$29,900
4 ሰው$33,200
5 ሰው$35,900
6 ሰው$38,550
7 ሰው$41,200
8 ሰው$43,850
9 ሰው$47,850
10 ሰው$52,270
11 ሰው$56,690

5. በአሁኑ ሰዓት የሚኖሩት በመንግሥት ድጎማ በሚደረግለት ቤት ውስጥ ቤት ነው? ማስታወሻ: ለዚህ መመሪያ የተለዩ ከዚህ በታች ሰፍረዋል፡፡ ያሉበት ሁኔታ ታይቶ አሁንም ለቫውቸሩ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ማን ነው ዜጋ ሳይሆን ብቁ የሆነ?

የንዑስ 8 ቫውቸር ለማግኘት፣ ከቤተሰብዎ አባል መካከል ቢያንስ አንዱ የአሜሪካ ዜጋ መሆን አለበት ወይንም ዜጋ ሳይሆን ብቁ መሆን አለበት፡፡ ዜጋ ሳይሆን ብቁ የሆነ:

 • ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ ያለው)
 • ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ (በተማሪ ቪዛ ያሉትን አይጨምርም)
 • Department of Homeland Security የስደተኛ ወይንም የጥገኝነት ወረቀት የተሰጠው
 • ከኤፕሬል 1 1980 በፊት በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ መግቢያ የተሰጠው
 • በጠቅላይ አቃቤ ሕግ ለሕግ ጉዳዮች የሕዝብ መብትን ለማስጠበቅ የሚፈለጉ
 • በጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወደ መጡበት ሀገር እንዳይላኩ ለሕይወታቸው ወይንም ለነጻነታቸው የሚያሰጋ የተባሉ ግለሰቦች

የመኖሪያ ዋስትና መምሪያ (Department of Homeland Security) የመንግስት ተረጂ (public charge) ድንጋጌ እንዴት ማመልከቻዬ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል?

የDepartment of Homeland Security የ“public charge” ማለትም የኢምግሬሽን ባለስልጣናት አንድ ሰው ግሪን ካርድን (ወይም ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ የሚሆንበትን) ወይም ለመኖር ወደ ዩናይትድ ኢስቴትስ የሚገባበትን ፈቃድ ለማግኘት ብቁ መሆኑን የሚወስኑበትን ሁኔታ የሚቀይር ድንጋጌ አጠናቋል። የመንግስት ተረጂነት ድንጋጌውም ለመኖሪያ ቤት እርዳታ ለሚያቀርቡት ማመልከቻ ብቁነት ላይ ተፅዕኖ የለውም። ይሁን እንጂ፤ በአዲሱ ድንጋጌ ስር ማመለከቻ ወይም የመንግስት ጥቅማጥቅሞችን፤ የህዝብ ቤት ወይም የክፍል 8 (Section 8) የቤት እርዳታን የሚቀበል ሰው፤ ከፌብረዋሪ 24፤ 2019 በኋላ ምናልባትም በpublic charge ፈተና ስር ይገባ ይሆናል። የቤት ጥቅማጥቅሞችን መቀበልዎ እንዴት የስደተኛ ሁኔታዎን እንደሚጎዳ ጥያቄ የሚጠይቁ ከሆነ፤ በጉዳዩ ላይ እውቀት ያላቸውን የስደተኞች ጠበቃ እንዲያናግሩ እንመክርዎታለን።

የአካል ጉዳት ያለበት ግለሰብ ብያኔ ምንድን ነው?

የአካል ጉዳተኛ ተብለው የሚባሉት ቋሚ የአካል ወይንም የአእምሮ ጉዳት ካለብዎትና ይህም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት ለማከናወን የሚያውክዎ ከሆነ ነው:

 • ለራስዎ ጥንቃቄ ያድርጉ
 • በእጅና በእግር የሚሰሩ ስዎችን መስራት ካልቻሉ
 • ማየት ወይንም ማድመጥ
 • መብላት
 • መተኛት
 • መንቀሳቀስ
 • መግባባት
 • መተንፈስ
 • መማር
 • ማንበብ
 • ትኩረት ማድርግ
 • ማሰብ
 • መስራት

በደጋፊ የደህንነት ገቢ (Supplemental Security Income (SSI)) ወይንም የማህበራዊ ዋስትና ለአካል ጉዳተኞች ገቢ (Social Security Disability Income (SSDI)) ላይ ከሆነ ለንዑስ 8 ቫውቸሮች እንደ አካል ጉዳተኛ ይታያሉ፡፡ SSI ወይንም SSDI የማይቀበሉ የአካል ጉዳትን ለመለየት ተጨማሪ አማራጭ አለ፡፡ ይህ ሰነድ የሚጠየቀው ለቫውቸር በተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ለተቀመጠ አመልካቾች ብቻ ነው፡፡

እኔ በሽግግር ቤት ውስጥ ነው የምኖረው፡፡ ማመልከት እችላለሁ?

አዎ፡፡ የሽግግር ቤት በጊዜ ገደብ የተቀመጠ መርሃ ግብር በመሆኑ (ከቤቱ ቤተሰብዎ መውጣት የሚጠበቅባቸው የተቀመጠ ቀን አለ)፣ ቤተሰቦችዎ “በቋሚነት ነዋሪ” ናቸው ተብለው አይቆጠሩም እንዲሁም ለቨውቸሩ ብቁ ናቸው ማለት ነው፡፡

የምኖረው ዝቅተኛ ገቢ ለሚያገኙ በተዘጋጀ ቤት ውስጥ ነው ወይንም በቫውቸር መርሃ ግብሩ ውስጥ ተካትቻለሁ፡፡ በተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ እንድገባ ማመልከት ይኖርብኛል?

በአጠቃላይ በሕዝብ ቤት ውስጥ ወይንም በቫውቸር መርሃ ግብር ውስጥ ከሆኑ ለተጠባባቂ ዝርዝር ብቁ አይደሉም

ምናልባት ለተጠባባቂ ዝርዝሩ ብቁ ሊሆኑ የሚችሉት በሚኖሩበት ቤት ውስጥ ለመኖር የማይችሉባቸው ምክንያቶች ከታች ከተጠቀሱት አንዱ መሆኑን ማሳመን ከቻሉ ነው፡

 • የቤት ውስጥ ጥቃት
 • የቤቱ ደህንነትና/ተደራሽነት
 • የጥላቻ ወንጀሎ(ች)
 • የመንግሥት ጣልቃ ገብነት
 • የተፈጥሮ አደጋ

በአሁኑ ሰዓት በሕዝብ ቤት ወይንም በቫውቸር መርሃ ግብር የሚኖሩ ከሆነና በንዑስ 8 ለማመለከት እርግጠኛ ካልሆኑ በ 206-214-1300 ይደውሉ፡፡

ለማመልከት ብቁ ለመሆን በKing ካውንቲ መኖር አለብኝ?

በጭራሽ፤ አመልካቾች ለዚህ እድል ለማመልከት King ካውንቲ መኖር አይጠበቅባቸውም፡፡ ለማመልከት በዓለማችን የትኛውም ክፍል መኖር ይችላሉ፡፡ ምን እንኳ በKCHA ህጋዊ ክልል ውስጥ የማይኖሩ ቢሆንም እና የንዑስ 8 ቫውቸርን የማይቀበሉ ቢሆኑም የመርሃ ግብሩ ተሳታፊ ለመሆን የመጀመሪያው ዓመት መርሃግብር ላይ መሳተፍ ይኖርብዎታል፡፡ የKCHA ሕጋዊ ወሰን በKing ካውንቲ ማንኛውም ስፍራ ሆኖ የ Renton እና Seattle ከተሞች የራሳቸው የቤቶች ፕሮግራም ስላላቸው ከዚያ ውጪ የሆኑትን አካባቢዎችን ያካትታል፡፡

ሌላ የቤቶች አማራጭ አለ?

ስለ ሌላ የቤቶች አማራጭ መረጃ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ 2-1-1ላይ ይደውሉ ወይንም በKCHA ድረገጽን ይጎብኙ https://www.kcha.org/housing/resources/.

እነዚህ በአቅራቢያ የሚገኙ የቤቶች አስተዳደር አማራጮች ናቸው:

Main Office
600 Andover Park W.
Tukwila, WA 98188
Tel: (206) 574‑1100
Fax: (206) 574‑1104
TDD: (800) 833‑6388
Directions

Section 8 Office
700 Andover Park W.
Tukwila, WA 98188
Tel: (206) 214‑1300
Fax: (206) 243‑5927
Directions